Get Adobe Flash player

ነሐሴ 24, 2008 ዓ.ም.

የአማርኛና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት: ... እሁድ ከጠዋቱ 2 ተኩል እስከ 5 ተኩል...
Amharic & Spritual Teachings: Sunday 8:30 AM - 11:30 AM ...
የአካዳሚ እርዳታና የወጣት ፕሮግራም: .... ቅዳሜ ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት...
Tutoring & Mentoring Program: Saturday 2:00 PM - 6:00 PM...
በአዲሱ የማጥመቂያ ቦታም አገልግሎቱ ከሰኞ እስክ አርብ ይሰጣል።...
Featured News, Reports,
Updates & Forms
What's New
አዲስ፡ የወጡ፡ መረጃወች
By-Law of R.A.D.S.K-Mariam
Service Request Form
የአገልግሎት፡ መጠየቃ፡ ቅጽች።
ጋብቻቸውን የሚሞላ ቅጽ
(Marriage Form)
Baptismal Certificate Form
ለጸሎተ ፍትሐት  የሚሞላ ቅጽ 
(Wake Service Form )
Reports and Documents
የቤተክርስቲያናን፡ የተለያዩ፡ የውስጥ፡አሠራር፡ የሚገልጹ፡ መረጃዎች።

Administration
Documents
 

Auditors Report
Auditors Report
(Finacial Documents
)

 

 

Error
  • JLIB_APPLICATION_ERROR_COMPONENT_NOT_LOADING

     Announcement
 
ኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋህዶቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን
ነሐሴ ፫ ቀን ፳፻፰ ዓም/ AUGUST 9,2016 የወጣውን መግለጫ አስመልክቶ በዝርወት ካለችው
ከርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

ዋሽንግተን ዲሲ ነሐሴ ፲፩ ቀን ፳፻፰ ዓም/AUGUST 17,2016

ቁጥር/DSKETHIO 01/08/2016

“አፍህን ስለ ዲዳው ክፈት፥ ተስፋ ስለሌላቸውም ሁሉ ተፋረድ። አፍህን ክፍት፥ በእውነትም ፍረድ፤ ለድሀና ለምስኪን ፍረድ።” ምሳ፥፴፩፥፰- ፱

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

እኛ በርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዋሽንግተን ዲሲ የምንገኝ አባላት በቅርቡ በቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እዬተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በቅርበት እየተከታተልን እንገኛለን። ሕዝባዊ እንቅስቃሴውን ምክንያት በማድረግ እጅግ ዘግይቶ የወጣውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መግለጫም በጥሞና ተመልክተነዋል። ይህ መግለጫ በየቀኑ በመንግሥት ከሚሰማው ፕሮፓጋንዳ የተለየ ምንም ነገር እንደሌለው ያነበበው ሁሉ የሚረዳው ሀቅ ነው። መግለጫው የሀገሪቷን መሠረታዊ ችግር ያልተመለከተ፣ የሕዝቡን በደልና እሮሮ ያላጤነ፣ ከመሆኑም በላይ ቤተክርስቲያን ለተጎዳው፣ በመንግሥት ታጣቂዎች እየሞተና የህልውናው መሠረት እየተናጋበት ያለውን ብዙኃን ህዝብ የማይወክል ሆኖ አግኝተነዋል።

ቅዱስ አባታችን በመንግሥት ታጣቂ ኃይሎች የተገደሉት ወገኖቻችን በዚህ 9 ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ700 በላይ ሲሆኑ በከፍተኛ ሁኔታ የቆሰሉና በየእስር ቤት የታጎሩት በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው። ዛሬ ምድሪቱ በህፃናት፣ በወጣቶች፣ በሴቶችና በአረጋውያን ደም ከጨቀየች በኋላ እንኳን ይህንን ጭፍጨፋ ይቁም ለማለት አለመድፈርዎ በእጅጉ አሳዝኖናል። እንሆ አባቶቻችን በድፍረት ወጥታችሁ መንግሥትን ጭፍጨፋ ይቁም ብላችሁ ለመጠየቅ ስንት ሕዝብ ማለቅ አለበት? እዉነት ለመናገርስ የምትደፍሩት መቼ ነው? የሕዝባችሁን ጩኸት ለመጮህ የምትነሱትስ መቼ ነው?

ቅዱስ አባታችን የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት ፳፭ ዓመታት ከዛሬ ነገ ደግ ዘመን ይመጣል ብሎ በትዕግሥት ሲጠብቅ የነበረ ትልቅና አስተዋይ ሕዝብ ነው። መበደሉን መከፋቱን ፣ መቸገሩንና ብሶቱን ሁሉ በሆዱ ችሎ ኖሮ ዛሬ በቃኝ! መኖሬም መሞቴም አንድ ነው ብሎ ቢነሳ ቅዱስነትዎ የህዳሴው ግድብ ግንባታ እንዳይስተጓጎል ህዝቡ ብሶቱን ማሰማቱን ያቁም፤ ችግር ካለበት በህጉና በሥርዓቱ ለገዢዎቹ ያቅርብ ማለትዎ አምርረን እንድናዝን አድርጎናል። ህዝቡ ፳፭ ዓመታት ሙሉ በደሉን የሚገልጽበት የሰብአዊ መብቱ ተገፎ ፣ ለመኖር በሚያደርገው መፍጨርጨር በርሃብና በስደት በምድር የዱር አራዊት፣ በባህር የአሳ ነባሪ ቀለብ ሆኖ፣ በዓለም አደባባይ ከሰው ተራ ወጥቶ በተዋረደበት፣ የተዋህዶ ልጆች ማዕተባቸውን እንዲበጥሱ ተጠይቀው እምቢ ብለው አንገታችንን ቀንጥሱት እያሉ ክቡር መስዋዕትነትን በከፈሉበት፣ መላው ሕዝብ ለመብቱ በሚያደርገው ተጋድሎ በእስር ተንገላቶ ስቃይና ግርፋት እየወረደበት ባለበት፣ የሰው ልጅ ሕይወት በረከሰባት ምድር፣ የመኖር ተስፋ በጨለመባት፣ ዕለት ዕለት በሞት በሚሰቃየው ህዝብ ደም በረሰረሰች መሬት ላይ በደሉ ገንፍሎ ህዝቡ ለፍትህ አቤት! አቤት! አቤት! እያለ ሲጮኽ፣ ቅዱሳት አባቶቻችን ሞልቶ የገነፈለውን የግፍ ጽዋ መፍትሔ እንዲፈለግለት መንግሥትን ለመጠዬቅ መድፈር አልቻላችሁም።

በየቀኑ ህዝብ ላይ የጥይት እሩምታ ሲዘንብበት ቅዱስነትዎ በድፍረት ከህዝቧ ጋር በመቆም መንግሥትን ብረቱን አስቀምጦ፤ የህዝቡን ጥያቄ ተቀብሎ ለስላም ድርድርና ውይይት እንዲቀመጥ መጠየቅና ማሳሰብ ሲገባዎት በዚህ ምስኪን ሕዝብ ላይ አሳበዋል። ጥቂቶች በብዙኃኑ ላይ የሚፈፅሙት በደል የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ እያለ ቅዱስነትዎ ይህንን እንኳን እንዲሻሻል መንግሥትን ለመማፀን ድፍረቱ ሊኖሮት አልቻለም።

ስለዚህ በቅዱስ አባታችን አመራር ሥር ያላችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች በዚህ ፈታኝና ክፉ ቀን ከገጠመን የፖለቲካ፣ የኤኮኖሚና የማህበራዊ ቀውስ እንድንወጣ፣ ተገቢውን ሃይማኖታዊ አስተምህሮ እየሰጣችሁ ከብዙኃኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ወግናችሁ በከንቱ የሚፈሰው የሰው ደም ይቆም ዘንድ ከተበደለው ህዝብ ጋር ካልቆማችሁ በታሪክ ተጠያቂ እንደምትሆኑ መዘንጋት የለባችሁም።

ቅዱስ አባታችን ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ አስጨናቂና አስቸጋሪ ወቅት ማየት የሚፈልገው እንደ ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ሚካኤል ለነፃነትና ለእውነት የሚቆምለት አባት እንጂ ሞልቶ እንደተረፈው እንደመንግሥት ካድሬ ለሕዝቡ መከራና ሥቃይ ግድ ያጣ አባት አይደለም። መግለጫዎ መንግሥት እንኳን ድክመቴ ነው መሻሻል ይገባዋል ብሎ ያመነውን እንኳን እንደአባት ለመጠየቅ ያልደፈረ በመሆኑ መግለጫው ከመውጣቱ ያለመውጣቱ እጅግ በጣም የተሻለ እንደነበር ለማስታወስ እንወዳለን።

የተባበሩት መንግሥታት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ የተለያዩ የዓለም መንግሥታት ግድያው ይቁም እያሉ በሚጮሁበት በዚህ አሳሳቢ ሰዓት ቅዱስነትዎ ልማት ይቀድማል፣ የአባይ ግድብ ይደናቀፋል እያሉ ማወጅዎ በመንግስት ወታደሮች በጠራራ ፀሐይ በጥይት አረር በተቃጠሉት ወገኖቻችን ላይ እንደ ማፌዝ የሚቆጠር መግለጫ በመሆኑ በእጅጉ አሳዝኖናል።

በመጨረሻም ለቅዱስ አባታችንና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ ቅዱስ ሲኖዶስ፤ እኛ የርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የባለአደራዎች ቦርድና አባላት ምዕመናን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን አቤቱታዎችን ተፈጻሚነት እንዲኖራቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ እንዲያደርግ በእግዚአብሔርና የመናገር መብቱን በተነፈገው በኢትዮጵያ ህዝብ ስም እንጠይቃለን።

1. በቅዱስነትዎ ለሕዝብ ይፋ የሆነው መንግስት በሕዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ግድያ በደልና ሰቆቃ የላገናዘበና የሃይማኖት አባትነት ተልእኮውን ያልተወጣ መግለጫ ከቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ ተልዕኮ ጋር የማይመጣጠንና ስልጣንዋን ዝቅ ያደረገ በመሆኑ በአስቸኳይ በሕዝቡ ላይ እየደረሰ ያለው ግድያና እስራት እንዲቆም የሚጠይቅ መግለጫ እንዲወጣ፤

2. በየቦታው የሚገኙት ካህናት፣ ሰባኪያንና የመንፈስ አባቶች በሁሉም አካባቢ ያሉት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ለየአካባቢያቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት ይህ በግፍ የሚፈሰውን የሕዝብ ደም በአስቸኳይ እንዲያቆሙ አቤቱታ እንዲያቀርቡ፤

3. እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለማስቆም የሚካሄደውን የመንግሥት የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ ቆሞ የህዝቡ ጥያቄ ተገቢውን መልስ እንዲያገኝ ቤተክርስቲያን አስፈላጊውን ተፅዕኖ እንድታደርግ፤

4. ዛሬ ሕዝቡ ራበኝ፣ ጠማኝ፣ ተከፍቼአለሁ ተገፍቼአለሁ በማለቱ በየእስር ቤቱ የታጎሩትንና በአጠቃላይ ፍትህ በማጣት እየተሰቃዩ ያሉ የህሊና እስረኞች በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያን እንድትጠይቅ፣

5. በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ ለስብዓዊ መብት መከበር ሲታገሉ በመንግሥት ወታደሮች ለተገደሉት ቤተሰቦች መንግስት ተገቢውን ካሣ እንዲከፍል ቤተ ክርስቲያን በአጽንኦት እንድትጠይቅ፣

6. መንግሥት በማን አለብኝነትና በአባገነንነት ያመጣውን ይህ የፖለቲካ ቀውስ ለማስቆምና ዘላቂ መፍትሔ ለመፈለግ ነፃ ውይይት የሚካሄድበት፣ ሁሉም የህዝብ ክፍሎች የሚሳትፉበት በሀገሪቷ ላይ ካንዣበባት አስጊና አሳሳቢ ሁኔታ እንድትወጣ የሚረዳ አስቸኳይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ሽንጎ እንዲጠራ ፍትህ ባጣው፣ የሕግ የበላይነት በማያከብረው መንግሥት በጥይት እንደ ጠላት በሚገደለው ሕዝብ ስም እንድታሳሰቡ አጥብቀን እንጠይቃለን።

ለኢትዮጵያውን ወገኖቻችን በሙሉ፦

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው አምባገነናዊ መንግሥት የኃይል እርምጃ እየተወሰደባቸው በመሞት፣ በመታሰር፣ በመንገላታትና በመሰደድ ላይ ካሉት ወገኖቻችን ጋር አጋርነታችንና ደጀንነታችን ለመግለጽ እንዲሁም በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ የሚያደርሰውን ግፍና በደል ለማውገዝና በቃችሁ ለማለት በጋራ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንገኛለን። ስለዚህ ጉዳዩ  ያገባናል የምትሉ በአካባቢው የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና የችግሩ ተቃዋሚዎች፤ የሃይማኖት ተቋማትና ማህባራዊ ድርጅቶች በምናደርገው ተቃውሞ እንድትሳተፉ ጥሪአችንን እንድትጠባበቁ በአክብሮት እንጠይቃለን።

በጸሎታችሁ ኢትዮጵያያንና ቤተ ክርስቲያናችንን አስቡ
አገራችንን ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቅልን
ወስብሃት ለእግዚአብሔር


ግልባጭ    

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ                                            
በአካባቢው ለምትገኙ የሃይማኖት ድርጅቶች
ለሰብአዊና ማህበራዊ ድርጅቶች
ለሁሉም ኢትዮጵያውያንና የችግሩ ተቃዋሚዎች

በዝርወት ላይ ያለች የርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የባለ አደራወች ቦርድ

 

ቤተ ክርስትያናችንን በፊታውራሪነት የበጠበጧት ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ በኢትዮጵያ ውስጥ ላደረሱት ተመሳሳይ የመከፋፈል ትምህርት ና ብጥብጥ ከአጥቢያ ቤተ ክርስትያኑ የተሰጧቸው ደብዳቤዎችን ይመልከቱ

ልዩ የ2008/2016 ዓ.ም የጾመ ሐዋርያት የጸሎት መርሐ ግብር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“መንገዳችንን እንመርምር እንፈትን፣ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ”
ሰቆቃወ ኤርምያስ 3፦40
 
“እግዚአብሔር ሆይ ወዳንተ መልሰን፣ እኛም እንመለሳለን ። ዘመናችንን እንደቀድሞ አድስ”
 
ሰቆቃወ ኤርምያስ 5፦20
 
ሰኔ 13 2008 የምንጀምረውን የጾም ወቅት ለሀገራችንንና ለቤተ ክርስቲያናችን፣ በተለይም ለአጥቢያችን እተካሄደ የአለውን የፍርድ ቤት ጉዳይ በሚመለከት፣ በምንኖርበት አገርና በመላው ዓለም ላይ ያተኮረ የጾም የጸሎት መርሐ ግብር እንዲኖረን እንድናደርግ የቀረበ አባታዊ ማሳሰቢያ፣ >> ወደ ሙሉ ዘገባ ይሀን ይጫኑ
 

----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

የርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባሎች በሙሉ

“አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም።” ፩ የዮሐንስ መል፦ ፪፥፬

 

የርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 28 ዓመታት ብዙ የተደከመባት፣ መስዋዕት የተከፈለባት አገልጋዮች በጎልበታቸው፣ በእውቀታቸው፣ በገንዘባቸው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በስደት በዚህ በሚኖሩበት ሀገር መከበሪያቸው፣ መጽናኛቸው፣ ቅርሳቸው፤ ለነገው ትውልድ የማንነቱ መገለጫና ማስረጃ እንድትሆን የተመኟትና ያዘጋጇት ቤተ ክርስቲያን ነበረች። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ተስፋ ያደረጓት፤ በርካታ መንፈሳዊና ማህበራዊ አገል\ግሎቶች ያበረከተች አንጋፋ ቤተ ክርስቲያን ነበረች። ሁላችሁም እንደምታውቁትና እንደሰማችሁት በዶር አክሊሉ ሀብቴ ሊቀመንበርነት፣ በአዲሱ አበበ አቀነባባሪነት፣ በቄስ ዘላለም አንተነህ ተላላኪነትና በጥላዋ ተጠልለው ቀን የውጣላቸው፣ ከሁሉ በላይ መስቀሉን በተሸከሙ ዘመናይ ካህናት አጃቢነት ያ ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለበት የዛሬ 8 ወር በአራት ተከታታይ እሑዶች ሁውከትና ረብሻ ሥርዓትና ደንቡን ንደው ሁሉንም እናዳልነበረ አደረጉት። >

 


 

 DSKMariam  Live 
 

የምስል መሕደር

 

በሊቢያ ለተሰውት ሰማዕታት የተደረግ ጸሎት

በሊቢያ ለተሰውት ሰማዕታት የተደረግ ጸሎት 

 

...ጥቂት ይታገሱኝ አየጫንኩ ነው...

የአገልጋዮች ውይይት

የአገልጋዮች ውይይት ተካሄደ 
መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሰሩ

 1ኛ ጴጥ 2 ቁ. 6

የርእሰ አድባራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በልዩ ልዩ ዘርፎች የሚያገልግሉ አገልጋዮች ሁለተኛውን የአገልጋዮች ስብሰባ ሕዳር 6 ቀን  ቀን 200 7 (November 15, 2014)  ዓ/ም ተካሄዷል። በስበሰባው ላይ በልዩ ልዩ ክፍሎች የሚያገለግሉ  ካህናትና ምዕመናን የተገኙ ሲሆን በቤተ ክርስቲያኗ ሁለንተናዊ  አገልግሎት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

የባለአደዋዎች ቦርድ በመራው በዚህ የሁለተኛው ግማሽ ዓመት የአገልጋዮች ስብሰባ ስለ አዲሱ ሕንጻ ግንባታ ሒደት፣ የባንክ ብድር ሒደትና በሌሎች ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ተስጥቷል። ከጉባኤው ተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶችም ተስተናግደዋል።

በእለቱ  “መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ”  በሚል ርዕስ በመጋቤ ሃይማኖት ተስፋዬ መቆያ አገልጋዮች መንፈሳዊ አገልግሎት ለማገልገል  በመንፈሳዊ ሕይወት መሠራት እንዳላባቸው የሚያስገነዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል።

...ጥቂት ይታገሱኝ አየጫንኩ ነው...
 
 
 

የቅዳሴ አገልግሎት

በርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የሕዳር ጽዮን  በዓለ ንግሥ በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናት አባቶች፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን እና ከሁለት ሺህ በላይ ምዕመናን  በተገኙበት  የተከበረው ይህ በዓል   በዓመት ውስጥ በበዓለ ንግሥ ከሚከበሩት አራት የእምቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓላት አንዱ ነው። 
 
ከሌሊት 6 ሰዓት (12am) በማኅሌት የተጀመረው የሕዳር ጽዮን በዓለ ንግሥ በሦስት መንበር  የተቀደሰውን የቅዳሴ አገልግሎት ጨምሮ ስብከት ወንጌል፣  የሊቃውንት ዝማሬ፣ የፍቅር ሕብረት ሰንበት ት/ቤት ዝማሬ እና ሌሎች አገልግሎቶችን አካቶ ከቀኑ በ7፡00 ሰዓት     (1፡00 pm)  ተጠናቋል;
 
በእለቱ የተከናውኑት ክንውኖች በአራት ክፍለን በፎቶ የተደገፈ ሪፖርት እነሆ።
 
1. የማኅሌት አገልግሎት   2. የጥምቀት አገልግሎት   3. የቅዳሴ አገልግሎት   4. በዓለ ንግሥ
 
...ጥቂት ይታገሱኝ አየጫንኩ ነው...
 
 

 በዓለ-ንግሥ 

 

 

Copyright DSK Mariam © 2015. All Rights Reserved.                                                                                                                                          የፌስ ገጻችን ተከታይ ይሁኑ